=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ምቀኝነት እንደ ምስጥ አጥንትን የሚሰረስር ነው። ምቀኝነት በእርግጥ አካልን የሚያጠፋ በሽታ ነው። እንደ ተባለውም ምቀኛ ምንጊዜም እረፍት የለውም የተበዳይ ካባ ለብሶ የሚኖር በደለኛ እና ጓደኛ መስሎ የሚኖር ጠላት ነው። ቀደምቶች እንዳትሉም ምቀኝነት ምስጋና ይገባው ለፍትሐዊነቱ አስቀድሞ ምቀኛን ማጥፋቱ።
እኔ ራሴንና አንተን ከምቀኝነት እከለክላለሁ ፤ ይህም ከሌላው በፊት ለራሴና ለአንተ ካለኝ እዝነት ነው። ምክንያቱም እኛ በሌላው በመመቀኘታችን ለጭንቀት ስጋችንን እናበላዋለን ፣ ለትካዜም ደማችንን እናጠጣለን ፣ ጣፋጩን እንቅልፍፋችንንም ለሌሎች እናከከፋፍላለን።
የምቀኛ ምሳሌው የጋለ ምድጃ ለኩሶ ራሱ እንደሚገባበት ነው። እረፍት ማጣት ፣ ድብርትና ጭንቀት ምቀኝነት የሚወልዳቸው በሽታዎች ናቸው። እረፍትንና ውቧን የተረጋጋችውን ህይወት ይበክላታል።
የምቀኛ ጥፋቱ መለኮታዊውን ፍርድ አለመቀበሉ ብቻ ሳይሆን ፈጣሪን በማዳላት መወንጀሉ ፣ ህጉን አለማክበሩና በነደፈው ስርዓት አለመታዘዙ ነው።
ምቀኝነት ምንኛ የከፋ ምንዳ የማይገኝበት በሽታ ነው። ምቀኛም እስኪሞት ድረስ ወይም ሰዎች ፀጋዎቻቸውን እስኪያጡ ድረስ እንደተቀጠለ ይኖራል። ምቀኛ ሲቀር ከሁሉም ሰው ጋር እርቅ ይፈፅማሉ ምክኒያቱም ከሱ ጋር ለመታረቅ አሏህ ከሰጠህ ፀጋዎች በሙሉ መላቀቅ አለብህ ፤ ችሮታዎችህንም መተው አለብህ ፤ ደረጃህንና እውቀትህንም መራቅ አለብህ። እነዚህን ካደረክ ምናልባት ቅር እያለውም ቢሆን ሊቀበልህ ይችላል። ከምቀኞች ምቀኝነት በአሏህ እንጠበቃለን ምክኒያቱም እንደ መርዛማ ጥቁር እባብ ንፁህ በሆነ አካል ውስጥ መርዙን እስኪረጭ እረፍት አያገኝም።
በመሆኑም አደራህን ከምቀኝነት ራቅ ፤ ከምቀኞችም በአሏህ ተጠበቅ ፤ እነሱ የትም ብትሆን ይከተሉሃልና።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|